ፍትህ – ለህፃን መሐመድ አብዱላዚዝ የህያ

ይድረስ ለተወደዳችሁ የንባብ ለሁሉም የፌስ ቡክ አምድ ታዳሚዎች፣ ሰላም እና ጤና ለእናንተ ይሁን። ዛሬ ሁላችንም በአንድ ድምፅ ልናስተጋባው የሚገባ የፍትህ ጥያቄ ስለገጠመኝ፣ ለዚሁ ትብብራችሁን ልጠይቅ ወደ እናንተ መጥቻለሁ። እናንተም እንደማታሳፍሩኝ የፀና እምነት አለኝ። ሼር በማድረግ፣ በአካልም የምትችሉ በቦታው በመገኘት፣ በተለያየ የዓለም ክፍል የምትገኙ የህግ ሰዎች ህጋዊ ድጋፍ አድርጉ!!
ፍትህ – ለህፃን መሐመድ አብዱላዚዝ የህያ

መሐመድ አብዱላዚዝ የህያ የተባለው ህፃን በሳውዲ አረቢያ ከኢትዮጵያውያን ወላጆች ከአስራ ሁለት አመታት በፊት የተወለደ ሲሆን በወቅቱ የመተንፈስ ችግር አጋጥሞት ህክምና ለማድረግ ወደ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን በህክምና ስህተት ለከፋ ችግር ተዳርጎአል።

ይህ ህፃን ራሱን ሳያውቅ ያለፉትን አስራ ሁለት በሆስፒታል አልጋ ላይ በህክምና መርጃ መሳሪያ እየተረዳ ይገኛል። እንደ ህፃን ሳይሮጥ እማ አባ ሳይል ይህው የህፃንነቱ ዘመን እያለፈ ይገኛል። እናትም ልጄ ከዛሬ ነገ ነቅቶ አየዋለሁ በማለት ከልጃቸው አልጋ አጠገብ ዘመናት እያሳለፉ ይገኛሉ። ከሦስት አመት በፊት ፍርድ ቤት ለደረሰው ችግር የህክምና ተቋሙ 2.4 ሚሊዮን የሳውዲ ገንዘብ የካሳ ክፍያ እንዲፈፀም ቢያዝም፣ ተቋሙ ክፍያውን የምፈፅመው ልጃችሁን ከዚህ ካወጣችሁ ብቻ ነው ብሎ አሻፈረኝ ብሏል። ይህ ድርጊት ፍፁም ኢሰባአዊ ነው። ማንም ወላጅ ልጁን በገንዘብ አይለውጥም፣ ካለመርጃ መሳሪያ መኖር የማይችል ህፃን ለመግደል የሚደራደር አይኖርም።
በዚህ ቤተሰብ ላይ የደረሰው በደል ተደራራቢ ነው።
1. ይህ ቤተሰብ ተበታትኖ ሁለት ቦታ እንዲኖር ተገዷል። እናት ልጄ ከዛሬ ነገ ይነቃል ተስፋ አልጋው አጠገብ ተቀምጠው አስራ ሁለት አመታትን ገፍተዋል። የእናትነት ፍቅር አሸንፎአቸው ኑሮአቸውን ጥለው ህክምና ማእከል ውስጥ ይገኛል፣ ይህ ሁኔታ የሚፈጥረው የልብ ስብራት ታላቅ ነው።
2. በተጨማሪም ሁለት ቦታ በመኖራቸው ምክንያት ተጨማሪ ወጭን የሚያስከትል ከመሆኑም በላይ፣ ትዳራቸውን በተገቢው መንገድ እንዳይመሩ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም።
3. በሃይማኖታዊ መለኪያም ይሁን ከሰባዊነት አንፃር የልጃችሁን ህይወት በገንዘብ ልግዛችሁ የሚል ተቋም መኖሩ አሳዛኝ ነው።
በመሆኑም ወገኖቼ ባገኘነው አጋጣሚ ሁሉ ይህን ጉዳይ በማስተጋባት ፍትህ የሚገኝበትን መንገድ እንድንደግፍ አደራዮ የላቀ ነው!!
በአሜሪካ እና አውሮፓ ያላችሁ የህግ ሰዎች እባካችሁ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ሙያዊ ድጋፍ እንድታደርጉ በፈጣሪ ስም ጥሪዮን አቀርባለሁ!!
ፍትህ ድምፃቸው ጎልቶ ለማይሰማ!!!

Leave a Comment:

SCROLL TO TOP